በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን ሴቶችን የሚደገፍ ሰልፍ በበርሊን እና በሌሎች የዓለም ከተሞች ተካሄደ


የኢራንን መንግስት የተቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀርመን ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል ።
የኢራንን መንግስት የተቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀርመን ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል ።

በዓለም የተለያዩ ቦታዎች ከተደረጉት ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው እንደተሰታፈበት የተነገረለት ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያንን ጨምሮ ወደ 80ሺ የተገመቱ ሰዎች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን ፣ በርሊን ተካሄዷል። ሰልፉ በኢራናዊያን ሴቶች ለተመራው ተቃውሞ አብሮነትን ማሳየት ዓላማው እንደሆነ ተነግሯል።

በሲውድን ፣ ጣልያን ፣ ፈረንሳይ ሲውዘርላንድ እና በሌሎች የአውሮፓ ከተሞችም ሰልፎች መደረጋቸውን የሚሳዩ ምስሎች ወጥተዋል። በለንደን፣ ቶሮንቶ፣ ዋሺንግተን እና ሎስ አንጀለስም ተጨማሪ ሰልፎች ተደርገዋል ።

በበርሊን በነበረው ሰልፍ ላይ ማሩ የተባለች የሰልፉ ተሳታፊ " እዚህ ቦታ የተገኘነው ለኢራን ህዝቦች 'አብራናችሁ ነን' ለማለት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ!” ብላለች ።ሌሎች ለቪኦኤ ሀሳባቸውን የገለጹ የሰልፉ ተሳታፊዎች “ በኢራን ጎዳናዎች ህይወታቸውን ለሚያጡት ሁሉ አብሮነታቸውን ለማሳየት በማሰብ ለሰልፍ እንደወጡ አስታውቀዋል።ከኢራን ውጭ በርካታ ኢራናዊያን በሚኖሩባት ሎስ አንጀለስ ሰልፈኞች የጋራ የእግር ጉዞ ያደረጉ አድርገዋል።ለኢራን መንግስት ውድቀትን ተመኝተዋል፣ “ ነጻነት እንሻለን !” በማለት በጋራ ጥሪ ሲያቀርቡም ተሰምተዋል።

ስድስተኛ ሳምንቱን የያዘው ፣እየበረታ የመጣው ሴቶች የመሩት ተቃውሞ የተነሳው ማሀሳ አሚኒ የተባለች ወጣትን ሞት ተከትሎ ነው። የሀገሪቱ አወዛጋቢ የአለባባስ ደንብ በመጣስ በመስከረም አጋማሽ በኢራን ስነ-ስርዓት አስከባሪ ፖሊሶች የተያዘቸው ማሀሳ ከሶስት ቀናት በኃላ በእስር ላይ እንደለች ህይወቷ አልፏል።

XS
SM
MD
LG