በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ሸባብ በሶማሊያ ወደብ ከተማ የሚገኝ ሆቴልን አጠቃ


ኪስማዩ/ ሶማሊያ
ኪስማዩ/ ሶማሊያ

የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ቡድን በሶማሊያ ደቡባዊ የወደብ ከተማ ኪስማዩ የሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ ጥቃት መክፈቱን እማኞች ተናገሩ።

እኩለ ቀን ገደማ “ታዋቃል” ከተባለው ሆቴል ፊት ለፊት አስቀድሞ የፍንዳታ ድምጽ ከተሰማ በኃላ ፣ የታጠቁ ሰዎች ሆቴሉን ጥሰው እንደገቡ ተነግሯል።

እማኞች እንደተናገሩት እንዲሁም ከስፍራው የተገኙ ቪዲዮዎችም እንደሚያሳዩት በሆቴሉ አቅራቢያ በጥቃት አድራሾች እና በጸጥታ ኃይል አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል ። የአደጋ ጊዜ ርዳታ ሰጪ መኪኖች (አምቡላንሶች ) ሆቴሉ ወደ ሚገኝበት የኪስማዮ ወደብ ጎዳና ሲያመሩም ታይተዋል።“ታዋቃል ሆቴል” በአካባቢው ሽማግሌዎች እና የንግድ ማህበረሰብ መሪዎች የሚዘወተር ስፍራ እንደ ነበርም ታወቋል።

በጥቃቱ በትንሹ 3 ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። አል-ሸባብ የተባለው የታጣቂዎች ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።

XS
SM
MD
LG