በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሜሎኒ የጣልያን ጠ/ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ


አዲሷና የመጀመሪያዋ የጣልያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጃ ሜሎኒ (ፎቶው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተወሰደ ነው)
አዲሷና የመጀመሪያዋ የጣልያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጃ ሜሎኒ (ፎቶው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተወሰደ ነው)

በጣሊያን የቀኝ አክራሪው ፓርቲ መሪ የሆኑት ጆርጃ ሜሎኒ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

መንግሥታቸው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጣልያን የመጀመሪያው የቀኝ አክራሪ መር መንግሥት ይሆናል ሲል አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በፕሬዚዳንታዊው ቤተመንግሥት ከፕሬዚዳንቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙት ሜሎኒ “የጣልያን ወንድሞች” የተሰኘው ፓርቲያቸውን ከተባባሪዎቻቸው ጋር ሆነው የመሰረቱት የዛሬ አስር ዓመት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ባላፈው ወር ምርጫ ትልቅ ድምጽ ማሰባሰብ የቻለው የጣልያን ወንድሞች ፓርቲ የኒዮ ፋሽስት መሰረት ያለው ሲሆን ከሌሎች ቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች ጋር የተቀናጀ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG