በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪፐብሊካን ፓርቲ ጉጉልን ከሰሰ


የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮና መክዳንኤል ወጥታችሁ ምረጡ በሚለው የቅስቀሳ ዘመቻ፣ እኤአ ጥቅምት 8/2015 ሰልፍ ታምፓ ፍሎሪዳ
የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮና መክዳንኤል ወጥታችሁ ምረጡ በሚለው የቅስቀሳ ዘመቻ፣ እኤአ ጥቅምት 8/2015 ሰልፍ ታምፓ ፍሎሪዳ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሪፐብሊካን ፓርቲ ብሄራዊ ኮሚቴ ከጥቅምቱ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫ በፊት የሚደረጉ የምርጫ ዘመቻዎችና የገቢ ማሰባሰቢያ ኢሜል ልውውጦችን እያፈነ ነው፥ ሲል በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል ላይ ክስ መስርቷል፡፡

ትናንት ዓርብ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተመሰረተው ክስ ንብረትነቱ የጉጉል በሆነው የኤሜል መልዕክት መለዋወጫው ጂሜል አማካይነት ድርጅቱ በሪፐብሊካን ፓርቲ ላይ ፍትሃዊ ያልሆነና አድሏዊ ተጽእኖ ይፈጽማል ብሏል፡፡

በተለይም በምርጫ ወቅት ተለዋዋጭ ድጋፍ በመስጠት በሚታወቁት ወሳኝ ክፍለ ግዛቶች የሚገኙ መራጮች ላይ የሚደረገውን የገቢ ማሰባሰቢያ እና ወጥታችሁ ምረጡ የሚሉ ጥሪዎችን እንደ ብልሹ መልዕክቶች በመፈረጅ ወደ መጣያው ቅርጫት (ስፓም) ውስጥ በመክተት በፓርቲው የምርጫ ዘመቻ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ሲል ከሷል፡፡

የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ ሌቀመንበር ሮና መክዳንኤል ለአሶሴይትድ ፕሬስ በላኩት መግለጫ “ከእንግዲህ ይበቃል ሪፐብሊካኖች ላይ እያሳየ ላለው ግልጽ አድልዎ ጉጉልን እየከሰሰን ነው” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ጉግል ክሱን ያስተባበለ ሲሆን ፖለቲካዊ ወገንተኝነትን መሰረት በማድረግ የኢሜል ልውውጦችን አያጣራም ብሏል፡፡

የጉጉል ቃል አቀባይ የጄሜል ስፓሞች የሚያመልከቱት የተጠቃሚዎችን ምርጫና እርምጃ ነው ማለታቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG