በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (አርብ) መረጃ


የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (አርብ) መረጃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (አርብ) መረጃ

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከትናንት፣ ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ18 ወራት ለሚቆይ ጊዜ ጊዜያዊ የከለላ ፍቃድ እንዳላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

“በግጭት፣ በሰብዓዊ ቀውስ፣ በምግብ እጥረት፣ በጎርፍ፣ በድርቅ፣ እና በመፈናቀል ምክንያት ወደ ሃገራቸው መመለስ የማይችሉ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ያለው ሁኔታ እስከሚሻሻል በአሜሪካ መቆየትና መሥራት ይችላሉ” ብሏል የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ።

በዚህም መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እየኖሩ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የዚህ ለአንድ ዓመት ተኩል የሚቆይ ዕድል ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉና የጭካኔ አድራጎቶች ሊፈፀሙ የመቻላቸው ጉዳይ አሳስቦኛል” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጋር ዛሬ ሲወያዩ ነው።

በሌላ በኩል ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የሚደረገው ዓለምአቀፍ ጫና የቀጠለ ሲሆን የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት እንዲሁም የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ዛሬ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነቱ በቅርቡ ያበቃል” ሲሉ ትናንት በነበረ አንድ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል። መንገዱን ግን አላብራሩም።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG