በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሠተኞችን የያዘ ጀልባ ከአደጋ ተረፈ


ፎቶ ፋይል፦ ፍልሠተኞች ግሪክ ሌስቦስ ደሴት 9/2022
ፎቶ ፋይል፦ ፍልሠተኞች ግሪክ ሌስቦስ ደሴት 9/2022

የድረሱልን ጥሪ ሲያሰማ የነበረና 75 ፍልሠተኞችን ያሳፈረ ጀልባ ከአደጋ ታድገው በሠላም ወደ ውሃ ዳር ማውጣታቸውን የግሪክ የባህር ድንበር ተባቂዎች አስታውቀዋል።

የጠፉ ወይም የተጎዱ ሰዎች ወሬ እንዳልተሰማ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ከጀልባው የድረሱል ጥሪ እንደተሰማ ወዲያውኑ የፍለጋና ነፍስ አድን ሥምሪት እንደተካሄደ የባህር ድንበር ጠባቂዎቹ ተናግረዋል።

ስድሳ ዘጠኝ ወንዶችና 6 ሴቶችን ያሳፈረው ጀልባ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ወደብ ዛሬ ጠዋት ተጎትቶ መወሰዱን ባለሥልጣናት ተናግረው፣ ነገር ግን የተሳፋሪዎቹ ዜግነት ወይም ከየት ተነስተው ወዴት እየሄዱ እንደነበር መረጃው ለጊዜው የላቸውም።

በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ከአፍሪካ፣ እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነትና ድህነትን ሽሽት በግሪክ አድርገው አውሮፓ ለመግባት ይሞክራሉ።

አብዛኞቹ ከጎማ በተሰሩና በአየር በሚንፉ ጀልባዎች ከቱርክ ተነስተው ወደ ምሥራቅ ግሪክ ደሴቶች ያመራሉ። ሌሎች ደግሞ ተለቅ ባሉ የተሻሉ ጀልባዎች ተሳፍረው ግሪክን አልፍው በቀጥታ ወደ ጣሊያን ያመራሉ። ሁለቱም አማራጮች አደገኞች ናቸው ተብሏል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ 27 ፍልሠተኞች በግሪክ ውሃ ዳርቻ ሰምጠዋል።

በአንደኛው አደጋ 18 ሰዎች ከባሕሩ ሰጥመው ለህልፈት ሲዳረጉ በሁለተኛው አደጋ ደግሞ 100 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረች ጀልባ ስትሰምጥ 9 ሞተው 12 የደረሱበት አልታወቀም።

XS
SM
MD
LG