በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (ሃሙስ) መረጃ


የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (ሃሙስ) መረጃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

የሰሜን ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (ሃሙስ) መረጃ

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ የታሰበው የሠላም ንግግር የፊታችን ሰኞ ሊጀመር ቀን እንደተቆረጠለት የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን “የሠላም ንግግሩ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አሳውቆናል” ሲሉ በትዊታቸው አመልክተዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ንግግሩን ለማስጀመር አዲስ ቀን ስለመቁረጡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከህወሓት በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

በተያያዘ ዜና፣ በቀጠለው ጦርነት ሳቢያ መንግሥት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት የሚደርስበት ጫና እያየለ ሲሆን፣ በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ በጦርነቱ “በትግራይ ክልል በሲቪሎች ላይ የአየር ድብደባ ስለመፈጸሙ በርካታ ሪፖርቶች ደርሰውኛል” ሲል የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ የሰጠውን መግለጫ “የተጋነነ” ብሎታል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG