በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን በጎሳ ግጭት 15 ሠዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦ ብሉ ናይል ስቴት በተባለው የሱዳን ግዛት ውስጥ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ሰዎች ሞቱ፤ እአአ 09/20/2022
ፎቶ ፋይል፦ ብሉ ናይል ስቴት በተባለው የሱዳን ግዛት ውስጥ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ሰዎች ሞቱ፤ እአአ 09/20/2022

ብሉ ናይል ስቴት በተባለው የሱዳን ግዛት ውስጥ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት 15 ሠዎች መገደላቸውን የአካባቢው መሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ትናንት ተናግረዋል።

በሃውሳ እና በተቀናኙ የዋድ አል-ማሂ ጎሳ አባላት መካከል በመሬት ይዞታ ይገባኛል የተጀመረው ጭቅጭቅ ወደ ግጭት አምርቷል። አካባቢው የሚገኘው ሁከት ባልተለየው የሱዳን ደቡባዊ ክልል፣ ከመዲናዋ ካርቱም 500 ኪሜ ላይ ነው።

የኃይል ግጭቱ ትናንት፣ ከበድ ያለ የተኩስ ልውውጥ መስማታቸውንና ቤቶች በእሳት መጋየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

“ከባድ የተኩስ ልውውጥ ነበር፣ ቤቶችም ተቃጥለዋል” ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምሥክር ተናግረዋል።

በዋድ አል-ማሂ ክሊኒክ የሚሠሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የህክምና ባለሙያም ክሊኒኩ አስር አስከሬኖችን መቀበሉን ተናግረዋል። ሮሰሪስ በተባለ ከተማየሚገኝ የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑ ሌላ ግለሰብ ደግሞ 5 አስከሬኖችንና 10 ቁስለኞችን መቀበላቸውን ተናግረዋል።

አንድ የሃውሳ መሪ እንዳሉት ግጭቱ የተካሄደው የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ባልሉበት እና የምሽት ሰዓት እላፊም በተጣለበት ሁኔታ ነው።

በተመሳሳይ ቦታ ባለፈው ሳምንት በመሬት ይዞታ በተነሳ ግጭት 13 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 24 ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (ኦቻ) አስታውቋል።

እንደ ኦቻ መረጃ ከሆነ ግጭቱ ባለፈው ሐምሌ ከጀመረ ወዲህ 149 ሰዎች ሲገደሉ 124 ቆስለዋል።

65ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎችም ከመኖሪያቸው እንደተፈናቀሉ ተመድ ይገልጻል።

የሐምሌው ግጭት የተጫረው የሃውሳው ወገን የሲቪል አስተዳደር ጥያቄ በማቅረቡና ይህም በታቃራኒው ወገን እንደ መሬት ፍለጋ ይዞታ ተደርጎ በመቆጠሩ ነው።

ግጭቱ በመላ ሱዳን የተቆጡ ሠልፈኖች ወደ አደባባይ እንዲወጡ ሲያደርግ፣ የሃውሳ ሰዎች ለተገደሉት ወገኖቻቸው ፍትህ እንዲሰጥ ሲሉ ጠይቀዋል።

ባለፈው ዓመት በሃገሪቱ ጦር ሠራዊት አዛዥ አብድል ፈታህ አል-ቡርሃን የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት ከተካሄደ በኋላ፣ ሱዳን እየጋመ በመጣው የፖለቲካ ግጭትና የኢኮኖሚ ቀውስ እየተናጠች ነው።

የመንግት ሥልጣን በወታደሩ በመነጠቁ፣ ያችን አገር ለ30 ዓመታት የመሩት ኦማር አል-በሺር የዛሬ ስት አመት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር የተያዘውን ጉዞ ገትቶታል።

XS
SM
MD
LG