በባሌ ዞን ሦስት ወረዳዎች በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አምስት ሰዎች መሞታቸዉን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ።
የባሌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ሴፈድን መሃመድ ወረርሺኑ በሦስት ወረዳዎች መከሰቱን ገልፀው አሁንም የጤና ባለሞያዎች የበሽታውን ወረርሺኝ ለመቆጣጠር ድጋፍ በመስጠት ላይ መሆናቸዉን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዩኤን ኦቻም በዞኑ የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ገልጿል።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]