በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ጦር አውሮፕላን ከተማ ውስጥ ወደቀ


በልምምድ ላይ ነበር የተባለ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ዪስክ በተባለች ከተማ መኖሪያ ሰፈር ውስጥ ወደቀ።
በልምምድ ላይ ነበር የተባለ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ዪስክ በተባለች ከተማ መኖሪያ ሰፈር ውስጥ ወደቀ።

በልምምድ ላይ ነበር የተባለ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ዪስክ በተባለች ከተማ መኖሪያ ሰፈር ውስጥ ወደቀ። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ ድረስ 14 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

አደጋው በአንድ መኖሪያ ህንፃ ላይ ከባድ እሳት ማስነሳቱም ታውቋል።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው፣ የአውሮፕላኑ አንደኛው ሞተር በእሳት የተያያዘው በልምምድ አገልግሎት ላይ በነበረበት ወቅት ነው። አብራሪዎቹና ሌሎች የአውሮፕላኑ ሰራተኞች የአደጋ ግዜ መስፈንጠሪያውን ተጠቅመው አውሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ራሳቸውን አትርፈዋል።

ከአዞቭ ባሕር አቅራቢያ የምትገኘው የዪስክ ከተማ ባለሥልጣናት እንዳሉት፣ አደጋው አንድ ባለ ዘጠኝ ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ከባድ እሳት ቢያስነሳም ከሰዓታት በኋላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው እና ቁጥሩ ዘጠና ሺህ የሚደርስ ህዝብ መኖሪያ የሆነችው ዪስክ ግዙፍ የሩሲያ ወታደራዊ አየር ጣቢያ መቀመጫም ነች።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው፣ አውሮፕላኑ ሱ-34 የተባለ ባለ ሁለት ሞተር ሱፐርሶኒክ ሲሆን፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ባላት ጦርነት እየተጠቀምርችበት መሆኑ ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለአደጋው እንደተነገራቸውና፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የክሬምሊን ቤተ መንግሥት አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG