በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን በጎሳ ግጭት አምስት ስዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦ ካርቱም፤ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፦ ካርቱም፤ ሱዳን

በሚሰሪያ እና በኑባ ጉሳዎች መካከል በምዕራብ ሱዳን በሣምንቱ መጨረሻ በተቀሰቀሰ ግጭት በጥቂቱ የአምስት ሠዎች ህይወት መጥፋቱን የሀገሪቱ ሠራዊት አስታወቀ።

ባለፈው አርብና ቅዳሜ ላጋዋ በተሰኘችው ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት የሀገሪቱ ጦር፣ የፈጥኖ ደራሽ የዕርዳታ ቡድንና ፖሊስ ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ሠራዊቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ሲል የሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ላጋዋ ከተማ የአማጽያኑ መሪ በአብደላዚዝ አል- ሂሉ የሚራው ‘የሱዳን ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ - በሰሜን’ የተሰኘው አንጃ በሚቆጣጠርበት አካባቢ ሲሆን፣ ወታደሮቻቸውም ውስጥ የኑባ ጎሳ አባላት የሆኑ እንደሚገኙበት ታውቋል።

ቡድኑ ለረጅም ግዜ ከሱዳን መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ የከረመ ሲሆን፣ የአረብ ሚሰሪያ አባላት በግጭቱ ተሳታፊ እንደነበሩ ተጠቁሟል።

ዘጠኝ የሚሆኑ የአረብ ጎሳ አባላት በሱዳን ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ - በሰሜን በተሰኘው አንጃ ተይዘው ከቆዩ በኋላ ባለፈው አርብ ካርቱም ገብተዋል።

የተለቀቁትም በአንጃው መሪዎች፣ በሱዳን ሉዓላዊ ም/ቤት መሪ አብዱል ፈታህ አልቡራን እና በደቡብ ሱዳን ገላጋዮች መካከል በተደረገ ድርድር መሆኑን ሠራዊቱ በሌላ መግለጫው አስታውቋል።

የመለቀቃቸውንም ጉዳይ “መልካም ፍላጎትን ያሳየ” ሲል ገልጾታል መግለጫው።

XS
SM
MD
LG