በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ከ725 ሚሊየን ዶላር በላይ ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች


ዩክሬን ኪየቭ 2022
ዩክሬን ኪየቭ 2022

ዋይት ሃውስ ትላንት እንዳስታወቀው አርብ ዩናይትድ ስቴትስ 725 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ትልካለች። ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ሩሲያ በዩክሬን ሲቪሎች ላይ መጠነ ሰፊ የሚሳይል ጥቃት ካደረሰች በኋላ ኪየቭን ለመርዳት የሚውል የመጀመሪያው ወታደራዊ ድጋፍ መሆኑን ዋይት ሃውስ አመልክቷል።

አዳዲስ ማጠናከሪያዎች እና የአየር መቃወሚያዎችን ከማካተት ይልቅ ኪየቭ ሩሲያን መልሳ ለማጥቃት በምታደርገው ዘመቻ የሚያግዙ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች የያዘ መሆኑንም የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

“እያቀርብናቸው ያሉት የሃይል ማጠናከሪያዎች በዩክሬን ጦር ሜዳዎች ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ናቸው” ሲሉ የዩናይትስ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አንተኒ ብሊንከን በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል።

XS
SM
MD
LG