በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ ውስጥ በደረሰ የአውቶብስ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፤ ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፤ ማሊ

በማዕከላዊ ማሊ ግዛት የተቀበረ ፈንጂ ላይ የወጣ አንድ አውቶብስ ባስከተለው አደጋ ቢያንስ 11 ሰዎች ሲሞቱ 53 የሚደርሱት ቆስለዋል ሲል የሆስፒታል ምንጮችን የጠቀሰው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ትናንት ዘግቧል፡፡

ፍንዳታው የደረሰው ሞፕቲ በተባለው አካባቢ ባንዲያጋራ እና ጎንዳካ ተብሎ በሚታውቁ ሥፍራዎች መካከል ባለ መንገድ ላይ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

አካባቢው በጅሃዲስቶች እንቅስቃሴ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚታወቅ መሆኑን ተነገሯል፡፡

በማሊ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ተልእኮ ማሊ ውስጥ በመሬት ላይ የተቀበሩ ፈንጂዎች እአአ እስከ ነሀሴ 31/2022 ድረስ 72 ሰዎች መግደላቸውን ሲገልጽ ባላፈው ዓመት 103 ሰዎች ሲሞቱ 297 ደግሞ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG