በያዝነው ዓመት በጦርነትና በሌሎች ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ምክንያቶች ሳቢያ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መነጠላቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 29 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ፣ የተመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ግን 23 ነጥብ 6 ሚሊዮን መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ለአሜሪካ ድምፅ አመልክቷል፡፡
በጦርነት ሳቢያ ከአራት ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውንና ከአንድ ሺህ ሦስት መቶ በላይ መውደማቸውን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚዋ እነዚህን ትምህርት ቤቶች የመልሶ ማቆም እና የጥገና ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም በተጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና፣ በመጀመሪያው ዙር ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን ገልፀዋል፡፡
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]