የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እአአ መስከረም 27/2022 ባደረገው ስብሰባ የኮሚሽኑን የሥራ ጊዜ በአንድ ዓመት ማራዘሙ ይታወሳል፡፡ ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ውሳኔውን እንደሚደግፍ እና ከኮሚሽኑ ጋር እንደሚተባበርም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ ሲል የገለጸውን የኮሚሽኑን ሥራ ዕድሜ መራዘም መቃወሙ ይታወቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አውስትራሊያ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ባወጡት መግለጫ “የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና የሰብዓዊ ቀውስ መባባስ በእጅጉ አሳስቦናል” ብለዋል።
“ኤርትራ ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድትወጣ” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የአንዳንድ ኃይሎች የተዛቡ ትርክቶች በጣም አስደንጋጭ ናቸው” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለዚህ የስድስቱ አገሮች የጋራ መግለጫ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የሰጡት ምላሽ የለም፡፡
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]