እአእ ከጥር 1/2023 ጀምሮ ለሦስት ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት እንዲያገለግሉ ከተመረጡ 14 አገሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ሞሮኮ እንደሚገኙበት ተገለጸ፡፡
47 አባላት ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ሲሆን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የህግ አሳሪነት የላቸውም፡፡
ሶማሊያ የተጣለባት የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲነሳላት ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ስትሆን፣ ኢትዮጵያ ኡጋንዳን በመከተል ድጋፏን ገልጻለች።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት በሶማሊያ ላይ የተጣለውን ከፊል የመሳሪያ ማዕቀብ ለማራዘም በመጪው ህዳር ወር ድምፅ ይሰጣል ተብሉ ይጠበቃል፡፡
ሶማሊያ ግን እስላማዊ አክራሪዎችን በተሻለ ለመዋጋት ትችል ዘንድ ማዕቀቡ መነሳት አለበት ባይ ነች።
ኢትዮጵያ ማዕቀቡ እንዲነሳ ድጋፍ የሰጠችው ባለፈው ሃምሌ እስላማዊ አክራሪዎች ድንበሯን አልፈው ገብተው ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ሶማሊያና ዓለም አቀፍ አጋሮቿ በአል-ሻባብ ላይ ከፍተኛ ጥቃት በማድረስ ላይ በሚገኙበት ወቅት ነው።