በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጭ ያሉ ኢራናውያንን የሃገር ውስጥ ተቃውሞ አስተባብሯቸዋል


ብራዚል የሚኖሩ ኢራናውያን አውራ ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ
ብራዚል የሚኖሩ ኢራናውያን አውራ ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ

በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና በሌሎች አገሮች የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን በተለያዩ የኢራን ከተሞች አራተኛ ሳምንቱን ያስቆጠረውን የጸረ መንግሥት ተቃውሞ በመደገፍ ወደ ጎዳናዎች መውጣታቸው ተነገረ፡፡

አብዛኞቹ የሰሞኑ ተቃውሞ የአገራቸውን ዕጣ ፈንታ ሊቀይር ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸውም የአሶሴይትድ ዘገባ አመልክቷል፡፡

እአአ ከ1979 የኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ፣ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የተሰደዱትና በምዕራባውያን ሃገሮች ዋና ከተሞች ተወልደው ያደጉት ብዙዎቹ የትውልደ ኢራን ማኅበረሰብ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች ህይወቷ ባለፈው የ22 ዓመቷ ሴት ሞት ምክንያት በአገር ውስጥ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በህዝቡ ዘንድ እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የዓላማ አንድነት መፍጠሩን ይናገራሉ፡፡

ኑሯቸውና ሥራቸው ለንደን የሆነው የ52 ዓመቷ ታህሪር ዳኔሽ “ይህ አጋጣሚ በብዙ መልኩ ኢራንን ሊለውጥ እንደሚችል አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡ ሁልጊዜም የሚከፋፍሉን የፖለቲካ ስህተቶች ነበሩ አሁን ግን ሰዎች “እኔ ከሴቶች ጎን ነኝ” እያሉ ነው፡፡” ሲሉ ለአሶሴይትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡

ዳኔሽ አያይዘውም “ይህ በጣም አስደናቂ ነው፣ በጣም በፍጥነት ነው በኢራናውያን መካከል ጓድኝት የታየው በጣምም ያስገርማል” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG