በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ኃይሉ ከበደ በዋስ ተፈቱ


የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ
የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ በዛሬው ዕለት በዋስ ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ፡፡

የፓርቲው የህግ ክፍል ኃላፊ አቶ ተስፋ ዓለም በርኸ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት፣ አቶ ኃይሉ ከበደ በዋስ እንዲፈቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነው ባለፈው ዓርብ ነበር፡፡

አቶ ተስፋ ዓለም እንዳሉት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መስከረም 16/2015 ዓ.ም አቶ ኃይሉ ከበደ በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ቢወስንም የፌዴራል ፖሊስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በመጠየቁ ሳይፈቱ ቆይተዋል፡፡

ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማፅናት በዋስ ከእስር እንዲፈቱ ዓርብ ዕለት በወሰነው መሰረት ዛሬ ተለቅቀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ከበደ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ ከቤት ከወጡ በኋላ የት እንደሆኑ እንደማያውቁ ፓርቲያቸው እና ቤተሰቦቻቸው ገልፀው የነበረ ሲሆን በኋላም በፌዴራሉ መንግሥት በአሸባሪነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ጳጉሜ 1/2014 ዓ.ም ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG