በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዕውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ አረፈ


ዕውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ አረፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:07 0:00

ዕውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ አረፈ

በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኝነት ለረጅም ዘመን ያገለገለው አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አቶ ፍቅሩ በሃገሪቱ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሐዘን መግለጫ መልዕክቱ አስታውቋል።

አቶ ፍቅሩ የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በራድዮ በማስተላለፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እንደነበረ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የስፖርት ዘገባዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረቡንም የፌዴሬሽኑ መግለጫው አስታውሷል።

ፍቅሩ ኪዳኔ ከጋዜጠኝነት በተጨማሪ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አመራር ውስጥ አገልግሏል፡፡

በቢስክሌት ፌዴሬሽን፣ በቴኒስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዋና ፀሐፊነት፣ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ማገልገሉንም የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴም በአመራርነት የሰራባቸው ተቋማት ናቸው።

"የፒያሳ ልጅ " እና "የስፖርት ጨዋነት ምንጮች" የተሰኙ መጽሐፍትንም አሳትሟል ።

ፍቅሩ ኪዳኔ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ከቆየ በኋላ ነው፣ በ88 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

በፍቅሩ ኪዳኔ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG