በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የነዳጅ ዋጋ እንዳይጨምር እርምጃዎችዋን እያጤነች ነው


የነዳጅ ዋጋ በካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ መስከረም 26/ 2015 ዓም
የነዳጅ ዋጋ በካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ መስከረም 26/ 2015 ዓም

ዩናይትድ ስቴትስ የነዳጅ ዘይት አምራችና ላኪ አገሮች ምርቶቻቸውን ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ በዓለም የነዳጅ ዘይት ዋጋ እንዳይጨምር ለመከላከል ተከታታይ እርምጃዎችን እያጤነች መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች አጋሮቹን ያካተተው የነዳጅ አምራችና ላኪ አገሮች ማህበራት (ኦፔክ) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዘይት ምርትን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በቀን በ2 ሚሊዮን በርሜል እንደሚቀንስ በመግለጹ ገበያው ላይ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቡድኑ ውሳኔ ቅር መሰኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ውሳኔውንም አርቆ ተመልካችነት የጎደለው “የአጭር ጊዜ እይታ ነው” ብለውታል፡፡

ዋሽንግተን እውቅና ከነፈገችው የቬንዙዌላ አምባገነን ሶሻሊስት መንግሥት ጋር አስተዳደራቸው ሊገናኝ ይችላል የሚሉ ዘገባዎችንም ባይደን “ምን ዓይነት አማራጮች ሊኖረን እንደሚችል እየተመለከትን ነው”ባሉበት ንግግራቸው ያረጋገጡት መምሰሉ ተነግሯል፡፡

ባለሙያዎች የነዳጅ ዘይት ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ እንዳይልኩ እንደ ቬንዙዌላና ኢራን በመሳሰሉ አገሮች ላይ የተጣለውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ማንሳት ተጨማሪ የነዳጅ ምርት ወደ ገበያው እንዲመጣ ያስችላል ይላሉ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚቀጥለው ወር ህዳር በሚደረገው ምርጫ፣ ምክር ቤቶቹን መቆጣጠር ለሚፈልጉት የፕሬዚዳንቱ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪዎች የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ጥሩ ዜና ሊሆን እንደማይችል ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG