በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካው የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ድርድር


የደቡብ አፍሪካው የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ድርድር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

የደቡብ አፍሪካው የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ድርድር

በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሠላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ህወሓት አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ለአፍሪካ ኅብረት ጥሪ ምላሽ በመስጠት ትናንት መስከረም 25/2015 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ “ተደራዳሪ ቡድናችንን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ተዘጋጅተናል” ብለዋል፡፡

ሆኖም “የሠላም ውይይት ጥሪ ከመቅረቡ በፊት ያልተመካከርንበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ማብራርያ ያስፈልገናል” ያሏቸውንም ነጥቦች አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም የአፍሪካ ኅብረት በደቡብ አፍሪካ የሠላም ንግግር እንዲጀመር ያቀረበውን ጥሪ መቀበሉን ትናንት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

“ሁለቱም አካላት ጥሪውን መቀበላቸው” ከአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ ተችሮታል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር፣ የሰላም ውይይቱ ይደረጋል ወደ ተባለበት ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሦስት ቀናት በፊት ማቅናታቸው ተዘግቧል፡፡

በተያያዘ አዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች “የአፍሪካ ኅብረት ዋናው የሽምግልና ቡድን በዩናይትድ ስቴትስ፣ በአውሮፓ ኅብረት፣ በተባበሩት መንግሥታት እና በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ወይም ኢጋድ ታዛቢዎች ይደገፋል” ብለዋል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG