በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነቱ በሰሜን ወሎና በዋግህምራ ዞኖች ጤና ተቋማት ውድመት መድረሱ ተገለጸ


በጦርነቱ በሰሜን ወሎና በዋግህምራ ዞኖች ጤና ተቋማት ውድመት መድረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00

በጦርነቱ በሰሜን ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች ጤና ተቋማት ውድመት መድረሱ ተገለጸ

ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም እንደገና የተጀመረውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተከትሎ በሰሜን ወሎ እና ዋግህምራ ዞኖች የሚገኙ በርካታ የጤና ተቋማት ወድመዋል ወይም ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የጦርነቱን እንደገና መጀመር ተከትሎ የህወሓት ታጣቂዎች በገቡባቸው የሰሜን ወሎና የዋግህምራ ዞኖች የወደሙ የጤና ተቋማትን በተመለከተ ጥናት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩንም የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ ገልፀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በበኩሉ “በህወሓት ታጣቂዎች ተይዘው በነበሩት በራያ በቆቦ እና አካባቢው አንድ ጠቅላላ ሆስፒታልና 13 ጤና ጣቢያዎች ለጥገና በማያመች ሁኔታ ወድመዋል” ብሏል።

ለዚህኛው ውንጀላ ከህወሓት በኩል የተሰማ ቀጥተኛ ምላሽ የለም። ከዚህ ቀደም የቀረቡበትን መሰል ውንጀላዎች ግን አስተባብሏል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG