በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡጋንዳ ውስጥ እስከ አሁን 11 ሰዎች በኢቦላ ሞተዋል


የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አራተኛዋ የጤና ባለሙያ በኢቦላ መሞቷን ትናንት አስታውቋል።
የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አራተኛዋ የጤና ባለሙያ በኢቦላ መሞቷን ትናንት አስታውቋል።

የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አራተኛዋ የጤና ባለሙያ በኢቦላ መሞቷን ትናንት አስታውቋል። እስከ አሁን 11 ሰዎች በበሽታው መሞታቸው ተነግሯል።

“የሱዳን ኢቦላ” የተባለው የበሽታው ወረርሽኝ ባለፈው ወር በኡጋንዳ የጀመረ ሲሆን፣ “የዛየር ኢቦላ” የተሰኘው ዝርያ ሃገር ውስጥ ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጣሬ ምርመራ በመካሄድ ላይ ነው።

የቪኦኤዋ ሃሊማ አቱማኒ ከካምፓላ እንደዘገበችው፣ የ58 ዓመቷ ማደንዘዣ ሰጪ የነበረችው የጤና ባለሙያ ለ17 ቀናት ከበሽታው ጋር ከተፋለመች በኋላ ትናንት አርፋለች። ማርጋሬት ናቢሱቢ ከሁለት ዓመት በኋላ ጡረታ የመውጣት ዕቅድ ነበራት።

የኡጋንዳ የህክምና ማኅበር ለጤና ባለሙያዎች በቂ የሆነና ራሳቸውን ከወረርሽኙ የሚከላከሉበት የህክምና ቁሳቁስ እንዲሰራጭ ጥሪ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ እስከ አሁን መልካም ምላሽ እያገኘ እንደሆነ አስታውቋል።

ኡጋንዳ የኢቦላ በሽታ መጀመሪያ በአንድ አውራጃ መግባቱን ያወጀችው መስከረም 10/2015 ሲሆን ከዛ ወዲህ ወደ አራት አውራጃዎች ተሰራጭቷል።

“የዛየር ኢቦላ” የተሰኘው የበሽታው ዓይነት ተከስቶ እንደሁ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴሩ ገና አላረጋገጠም። መገኘቱ ከታወቀ ከሶስት አመት በኋላ በድጋሚ ሊከሰት መሆኑ ነው። ለ“የዛየር ኢቦላ” በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ ክትባት የለም።

የሱዳኑ ኢቦላ መጀመሪያ የታየው በሱዳን ደቡባዊ ክፍል በእአአ 1976 ነው። ከዛ ወዲህ በሽታው ለበርካታ ግዜ ተከስቶ የነበር ቢሆንም፣ የከፋው ግን በእአአ 2000 በኡጋንዳ ተከስቶ የነበረውና የ200 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ነው።

XS
SM
MD
LG