በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ ተቃዋሚዎች የፈረንሳይ ኤምባሲን አጠቁ


በቡርኪና ፋሶ ተቃዋሚዎች የፈረንሳይ ኤምባሲን አጠቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

በቡርኪና ፋሶ ተቃዋሚዎች የፈረንሳይ ኤምባሲን አጠቁ

ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ውስጥ ትንናት እሁድ ከሰዓት በኋላና ምሽቱን በሙሉ ወደጎዳና የወጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች የፈረንሳይ ኤምባሲን አጥቅተዋል፣ ጎማዎችን ያቃጠሉ ሲሆን የሩሲያን ባንዲራ ሲያወለበልቡም ታይተዋል፡፡

ወታደራዊው ጁንታ ባላፈው ዓርብ በአገሪቱ ሥልጣን መቆጣጠሩን ቢያሳውቅም መላ አገሪቱን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረ አይመስልም፣ በከተማው ሁከት ነግሷል፡፡

ዋጋዱጉ ከሚገኘው ፈረንሳይ ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት እሁድ የፍንዳታና የተኩስ ድምጽ ተሰምቷል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወደኤምባሲው አጥር ተቀጣጣይ ነገሮችና ድንጋይ መወርወር ከጀመሩበት ምሽት በፊት አንስቶ የአገሪቱን ዋና ከተማ ጎዳናዎች ሲያጥለቀልቁ ቆይተዋል፡፡

ምንጩ ካልታወቀ አካባቢ ተቃዋሚዎች ፈረንሳይ የዓርቡን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እንድትቀለብስ ግፊት እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ ጥሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች እየቀረቡ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አዲሱ ወታደራዊ ቡድን እና የፈረንሳይ ኤምባሲ ፈረንሳይ መፈንቅለ መንግሥቱ ምንም ተሳትፎ የሌላት መሆኑን አስተባብለዋል።

የፈረንሳይ ኃይሎች ከኤምባሲው ውስጥ በመሆን ከደጅ ወዳሉ ተቃዋሚዎች የአስለቃሽ ጋዝና የማስጠንቀቂያ ተኩሶችን በመጠቀም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ቪኦኤ ያነጋገራቸው ከተቃዋሚዎቹ አንዱ የሆኑትን አሊ ናኔማን “እአአ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ከተሳተፍንበትና በተግባር የተደባለቀ ውጤት ካስገኘው የፈረንሳይ አጋርነት መውጣት አለብን፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታት ቀውስ ገጥሞናል፡፡ ከፈረንሳይ ጋር ያለን ትብብር ግን አጥጋቢ ውጤት አልሰጠንም፡፡ ሌላ ትብብር የሚያስፈልገን በዚህ ምክንያት ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ከኤምባሲው 300 ሜትሮች ፈንጠር ብሎ ካለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በተባበሩት መንግሥታ የጦር ተሽከርካሪ በመሆን ሲወጡ የታዩት የግልበጣው ተሳታፊ አባላት የሩሲያን ባንዲራ ሲያውለበልቡ መታየታቸው ሩሲያ የዓርቡን መፈንቀለ መንግሥት ሳትደግፍ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በብዙዎች ዘንድ እንዲነሳ አድርጓል፡፡

መሰረቱን በኔዘርላንድ ያደረገው የክሊንገንዴል ምርምር ተቋም ተንታኝ የሆኑት ኮንስታንቲን ጉዋቪሆን ተብሎ የተለቀቀው የሩሲያው የተሳሳተ መረጃ ቅዳሜና እሁድ ለተፈጠሩ ሁኔታዎች መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲገልጹ ተከታዩን ብለዋል።

“በማኅበራዊ ሚዲያ በስፊውየተሰራጩ አሳሳች መረጃዎችንና የሩሲያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተቃዋሞው ሲሳተፉ በቅርቡ ቀናት ተመልክተናል፡፡

ምንም እንኳ ሁሉንምነገር በሩሲያው አሳሳች ኢንፎርሜሽን ላይ ማሳበብ ባንችልም ተቃውሞውን በማቀጣጠል ምን ያህል ነዳጅ ጨምሯል፣ ያሳደረው ተጽእኖ ምን ያህል ነው ብሎ ለማለት አሁን ጊዜው ገና ነው፡፡ ከትናንት ጀምሮ፣ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶችና ቅሬታዎች ወደ ጎዳና ወጥተዋል፡፡

እየተባባሰ በመጣው የጸጥታ ሁኔታ ሰዎች ደስተኛ አለመሆናቸውን አይተናል፡፡ በጥር ወር የከሸፈውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የመሩ ዙንግራና፣ የግራ ዘመም ርዕዮተ ዓለም ደጋፊ የሆኑት ሳንካራውያንና እንዲሁም የሩሲያ ደጋፊዎች የሆኑትም ደግሞ አሉ፡፡”

የቡርኪና ፋሶን ባንዲራ ለብሰው ከኢምባሲው ውጭ የነበሩ አንድሰው ደግሞ “ሩሲያ መጥታ ከዚህ ውጥንቅጥ ታድነናለች፡፡ ምክንያቱም ከሩሲያ ጋር የሰሩት አገሮችሁሉ ተሳክቶላቸዋል፡፡

ይህ ሽብርተኞችን ለማሸነፍ ከተፈለገ ወደ ሩሲያ አቅጣጫ እንድንሄድ ያበረታታናል፡፡ ካለብን የደህንነት ችግር አንጻር ደሚባወደ ሩሲያ ይወስደናል ብለን አስበን ነበር፡፡ግን ስንጠብቅ የቆየነው በከንቱ ነበር፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡

በወታደራዊ ግልበጣ ወደ ሥልጣን የመጡት መሪዋ ከ9ወር ቆይታ በኋላ በሌላ ሁለተኛ መፈንቀለ መንግሥት በተወገዱባት ቡርኪና ፋሶ ሰላም እንዲሰፍን ክሬሚሊን ጠይቃለች፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲምትሪ ፔስኮቭ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በቡርኪና ፋሶ ያለው ሁኔታ በተቻለ ፍጥነት ወደ መደበኛ ሁኔታ እንዲመለስ፣ በአገሪቱ ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ እንዲረጋገጥ፣ የህጋዊነት ማዕቀፍ በአስቸኳይ እንዲመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

በቅርቡ የሩሲያው የቅጥር ወታደሮች ድርጅት ዋግነር ቡድን በጎረቤት አገር ማሊያለውን የጸጥታ ሁኔታ ላይ ስላመጣው ተጽእኖ የተጠየቁት ጉዋቪ

“በማሊ የዋግነር ተሳትፎ በሁሉም መለኪያዎች ነገሮች የበለጠ እንዲከፉ ያደረገነው፡፡” ብለዋል፡፡

የአገሪቱ ሁለተኛ ከተማ በሆነችውናበዋና ከተማው ውስጥ ያሉ የፈረንሳይ ተቋማትና በፈረንሳይ መንግሥት የሚመሩ የባህል ማዕከላት በተቃዋሚዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

ተቃዋሚዎች ፈረንሳይ ከሥልጣን የተወገዱትን ፕሬዚዳንት ፖል ኼንሪዳሚባን ከዋጋዱጉ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ አስጠግታለች የሚል የተሳሳተ ግምት አድሮባቸዋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG