በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት “ኃይሎቼን ከሰሜን ወሎ አስወጣሁ” አለ


ህወሓት “ኃይሎቼን ከሰሜን ወሎ አስወጣሁ” አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00

ህወሓት “ኃይሎቼን ከሰሜን ወሎ አስወጣሁ” አለ

ህወሓት ኃይሎቹን ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ማስወጣቱን ተናገረ። የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ “ሰራዊታችን በሌሎች ቦታዎች ያሉትን ሥጋቶች በተሻለ መንገድ ለመቋቋም ወደ ሌላ ቦታ እየተዛወረ ነው” ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት የውጭ ጉዳዮች ቢሮ የተባለ አካልም ባወጣው መግለጫ፣ በገዛ ፈቃዳችን “በደቡብ አቅጣጫ ከገባንባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በመውጣት የቦታ ለውጥ አድርገናል።” ብሏል።

ለዚህ የህወሓት መግለጫ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን በቀጥታ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ ይሁን እንጂ “ህወሓት በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ እና አካባቢው የሚያካሂደው ጥቃት፣ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ህዝብ ጠንካራ ምላሽ ምክንያት ባሰበው ልክ አልሄደለትም” ሲል መንግሥት ከዚህ ቀደም መገልጹ ይታወሳል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጦርነቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ የምታደርገውን ጥረት በመቀጠል የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኳን ከዛሬ ጀምሮ በድጋሚ ወደ አካባቢው እና ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡

ልዩ ልዑኩ ሀመር ከዛሬ መስከረም 23 ጀምሮ ለ15 ቀናት ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገልጿል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG