በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራኦሬ የገባንበት ትግል ለሥልጣን አይደለም አሉ


ትራወሬ ኡጋዱጉ ውስጥ የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መሪ ፖል ሄንሪ ሳንደአጎ ዳሚባና መንግስታቸው መወገዱን በቴሌቪዥን መግለጫቸው ባስታወቁበት ወቅት
ትራወሬ ኡጋዱጉ ውስጥ የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መሪ ፖል ሄንሪ ሳንደአጎ ዳሚባና መንግስታቸው መወገዱን በቴሌቪዥን መግለጫቸው ባስታወቁበት ወቅት

አዲሱ የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መሪ ካፕቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ከቡርኪና ፋሶ ኃይሎችና የተወገደውን ወታደራዊ ጁንታ ሊደግፉ ይችላሉ ከሚሏቸው ኃይሎች ጋር ግጭት መፍጠር እንደማይፈልጉ ለአሜሪካ ድምጽ ትናትንት ቅዳሜ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናገሩ፡፡

“ የገባንበት ትግል ለሥልጣን አይደለም” ያሉት ትራኦሬ “የምንመራው ትግል ለቡርኪናፋሶ ነው፡ ህዝባችንን መከላከል እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል ምልልስ፣ በአንዳንድ ቡርኪና ፋሶ አካባቢዎች “በዛፎቹ ላይ ያሉት ቅጠሎች በሙሉ ጠፍተዋል፣ ምክንያቱም ሰዎች እነዚያን ቅጠሎች እየበሉ ነው፡፡ ሰዎች ሳር ሳይቀር እየበሉ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ትራኦሬ አያይዘውም “ ለእነዚህ ሰዎች ለማምረትና ደህንንታቸውን መጠበቅ የሚያስችሉንን መፍሄዎችን እያቀረብን ነው፡፡ ብዙ መፍትሄዎችን አቅርበናል፡፡ ይሁን እንጂ አልተሰማንም፡፡ ብዙ መፍሄዎችዎን ብናቀርብም እንደመሰለኝ በመጨረሻው ላይ ፖለቲካ እየተጫወትን ነው፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡

ወታደራዊ ኃይሎች ባላፈው ዓርብ የወታደራዊ ጁንታ መሪ ናቸው ያሏቸውን የቀደሞ ወታደራዊ መሪ ፖል ሄንሪ ሳንደአጎ ዳሚባን እያደገ የመጣውን እስላማዊ አክራሪነትና አመጽን ማስቆም አልቻሉም በሚል ከሥልጣን ማስወገዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመፈንቅለ መንግሥት የተወገዱት ዳሚባም ሥልጣኑን የተረከቡት የቀደሞውን ፕሬዚዳንት ራች ማርክ ካቦሬን ባላፈው ጥር በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካስወገዱ በኋላ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬሽ በቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱጃሪክ በኩል ትናንት በሰጡት መግለጫ፣ በበሩኪና ፋሶ ያለው ሁኔታ ያሳሰበቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሥልጣንን በጠመንጃ ኃይል የመያዝ ሙከራን አውግዘው ሁሉም ተሳታፊ ወገኖች ከአመጽና ጥቃት ድርጊቶች ተቆጥበው ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ዋና ጸሀፊው አሳስበዋል፡፡

አዲሱ የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ “ ፕሬዚዳንት የምንመርጥበትን ብሄራዊ መድረክ እየተጠባበቅን ነው፡፡” ብለዋል ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ መጠየቅ፡፡

XS
SM
MD
LG