በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ቁልፍ የሆነችው ሊማንን ተቆጣጠረች


ሊማንን የተቆጣጠሩት የዩክሬን ወታደሮች
ሊማንን የተቆጣጠሩት የዩክሬን ወታደሮች

ዩክሬን የሩሲያው ፕሬዚዳን ባላፈው ሳምንት ወደራሳቸው ግዛት በኃይል ከቀላቀሏቸው ግዛቶች መካከል በምስራቃዊ ግዛት የምትገኘውን የሎጂስቲክ መናኻሪያ ሊማንን መቆጣጠሯን አስታወቀች፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ዛሬ እሁድ በቴሌግራም ማህበራዊ መድረክ ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልክዕክታቸው “ሊማን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሆናለች” ብለዋል፡፡

ሩሲያ ዛሬ እሁድ ስለጉዳዩ አስተያየት ባትሰጥም ትንናት ቅዳሜ በሰጠችው መግለጫ የዩክሬን ወታደሮች ከበባ ሊያደርሱ ይችላሉ በሚል ስጋት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ማስታወቋ ተዘግቧል፡፡

ሩሲያ አካባቢውን የተቆጣጠረችው ባለፈው ግንቦት ሲሆን ወደ ሰሜን ዶኔትስክ ግዛት ለምታደርገው እንቅስቃሴ የትራንስፖርት መናኻሪያ አድርጋ ትጠቀምበት እንደነበር ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG