በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሌላ መፈንቅለ መንግስት በቡርኪና ፋሶ

Members of Burkina Faso's army seized control of state television late Friday, declaring that the country's coup leader-turned-president, Lt. Col. Paul Henri Sandaogo Damiba, had been overthrown after only nine months in power. (RTB via AP)

በቡርኪና ፋሶ ጦሩ የመንግስት ሥልጣንን መቆጣጠሩን የጦሩ አባል የሆኑት ሻለቃ ኢብራሂም ትራኦሬ ትናንት ማምሻውን አስታውቀዋል። ከስምንት ወራት በፊት በሌላ መፈንቅለመንግስት ሥልጣን ነጥቀው የነበሩት የጦሩ መሪ ፖል ሄንሪ ዳሚባ ተመሳሳይ ዕጣ ደርሷቸዋል።

ሻለቃ ኢብራሂም በመግለጫቸው እንዳሉት፣ የዳሚባ ረዳት የነበሩት የጦሩ አባላት “እስላማዊ አክራሪነትንና አመጽን እየተዋጋች ያለችውን ሃገር ደህንነት ማስጠበቅ አልቻሉም ብለው ስላመኑ ውሳኔው ላይ ደርሰዋል።”

በሻለቃ ትራኦሬ የተፈረመውን የጦር መግለጫ አንድ ሌላ የጦር መኮንን በቴሌቭዥን ማንበባቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ቴሌቭዢን ዘግቧል።

ትናንት በመፈንቅለ መንግስት የተወገዱት ዳሚባ፣ ባለፈው ጥር ወር የቀድሞው ፕሬዝደንት ሮች ካቦሬን፣ እንዲሁ በመፈንቅለ መንግስት አስወግደው ስልጣኑን በእጃቸው ሲያደርጉ፣ የሀገራቸውን ደህንነት ሁኔታ አስተማማኝ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው ነበር። ሃገሪቱ ግን ወደ ብጥብጥ ማምራቷንና የፖለቲካ ውጥረት ማስተናገዷን ቀጥላ ነበር ተብሏል።

ዳሚባ በኒው ዮርክ በተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገው እንደተመለሱ ነበር፣ ወንበራቸው ተነጥቆ የጠበቃቸው።

አዲሶቹ ወታደራዊ መሪዎች የሀገሪቱን ብሄራዊ ሸንጎ አፍርሰው፣ ድንበሮችም ዝግ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የምሽት የሰዓት እላፊም ተጥሏል።

XS
SM
MD
LG