በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የሰብዓዊ ሁኔታ አሳስቦኛል" የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት


“በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የሰብዓዊ ሁኔታ አሳስቦኛል” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

“በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የሰብአዊ ሁኔታ አሳስቦኛል” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

“የሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባበት መንገድ እንደተዘጋ ቀጥሏል” ያሉት የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች “የግጭቶች መባባስ ሲቪሎችን ለተጨማሪ አስከፊ ችግር እንደሚዳርግም ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል ያለው መወነጃጀል አሁንም ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚሩባቸው አካባቢዎች በአየር እና በከባድ መሳሪያ እየፈጸሙ ነው ባለው ድብደባ፣ በርካታ ሰላማዊ ዜጎችን እየገደሉ ነው ሲል ህወሓት ከሷል፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት የውጭ ጉዳይ ቢሮ የተባለ አካል ባወጠው መግለጫ፣ የኤርትራ አየር ኃይል በአዲ-ዳዕሮ ጥቃት በመፈጸም፣ በርካታ ሰላማዊ ዜጎችን ገድሏል ብሏል።

የአየር ድብደባው የተፈጸመው በኢትዮጵያ አየር ኃይል መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በበኩሉ፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ተተኳሾች ያሉበትን ሥፍራ ዒላማ ያደረገ እርምጃ ወስዷል ብሏል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት በሚወስዳቸው እርምጃዎች በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሰም ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG