በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውዝግቦች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች


የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውዝግቦች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:07 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውዝግቦች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም ለመፍታት “ዝግጁ አይደለም” በሚል የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት መወነጃጀላቸውን ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት የሰላም ሂደት ባላት አቋም እንደጸናች ናት ብሏል፡፡

ህወሓትም በሕብረቱ የሚመራ የሰላም ሂደትን ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ያሳወቀ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለህወሓት እርምጃ እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም፡፡

ይህን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር መለስ ዓለም፣ የኢትዮጵያን አቋም ከማረጋገጥ ባለፈ ስለ ህወሓት እርምጃ ያሉት የለም፡፡ እስካሁን ለጦርነቱ ሰላማዊ መፍትሔ ማምጣት ያልተቻለው፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል መተማመነን ባለመኖሩ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ ዜና በዛሬው መግለጫቸው አምባሳደር መለስ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ እያደረጉት ሥላለው ጉብኝት አንስተው፣ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሥምምነቶች መደረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG