በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል የትምሕርት ቤቶች ውድመት ያስከተለው ፈተና


በቤኒሻንጉል የትምሕርት ቤቶች ውድመት ያስከተለው ፈተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:24 0:00

በቤኒሻንጉል የትምሕርት ቤቶች ውድመት ያስከተለው ፈተና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዚህ በ2015 ዓ.ም. ውስጥ ከ300 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቢያቅድም እስከ አሁን 122 ሺ የሚሆኑ ተማሪዎችን ብቻ መዝግቦ ትምህርት ማስጀመሩን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ቢንያም መንገሻ የሰላም ሁኔታ ቢሻሻልም ባለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው የጸጥታ ችግር ሳቢያ 287 ትምህርት ቤቶች በመውደማቸውና ለተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስ አለመሟላት ተማሪዎችን ከትምህርት አስተጓጉሏል ብለዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹን መልሶ ለመገንባትና ለተማሪዎችም ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

እስከ አሁን ተፈናቅለው ወደየአካባቢያቸው ያልተመለሱ ተማሪዎችም ባሉባቸው አካባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች እንደሚማሩ ሀላፊው አክለው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG