በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜኑ ጦርነት እና ያልተቋረጡት ውዝግቦች


ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ የተሰየመው የባለሞያዎች ኮሚሽን ሊቀ መንበር
ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ የተሰየመው የባለሞያዎች ኮሚሽን ሊቀ መንበር

በትግራይ ክልል የተፈጸመ የድሮን ጥቃት ፍንጣሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራምን አንድ የዕርዳታ መኪና መምታቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሮይተርስ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ላከልኝ ባለው የጽሁፍ መልእክት "በጥቃቱ ሳቢያ የተፈጠረ ፍንጣሪ በዓለም ምግብ ፕሮግራም ተቀጥሮ የሚሰራ አሽከርካሪ ጎድቷል" ብሏል።

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳም የመንግሥት ድሮኖች የዓለም ምግብ ፕሮግራምን የጭነት መኪና እንዳወደሙ እና ሹፌሩ እንደተጎዳ በመግለጽ ክስ አቅርበዋል፡፡

ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን በቀጥታ የተሰጠ ምላሽ የለም። የእርዳታ ድርጅቶች መንግሥት የመከላከል እርምጃ በሚወስዳቸው አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ግን አሳስቧል፡፡

በሌላ ዜና፣ በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ የተሰየመው የባለሞያዎች ኮሚሽን ሊቀ መንበር ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ከኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው፡፡

ሙሩንጊ የኮሚሽኑን የምርመራ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለተፈፀሙ አብዛኛው ወንጀሎች መንግሥትን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሰሜኑ ጦርነት ዳግም ካገረሸ በኋላ ስለጦርነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ጦርነቱን የቀሰቀሰው ህወሓት መሆኑን ገልጸው፣ “…ሀገራዊ ሕልውናችንን ለማስጠበቅ ስንል ወደ መከላከል እንድንገባ ተገድደናል” ብለዋል። ህወሓት በበኩሉ ለጦርነቱ መቀስቀስ ተጠያቂ የሚያደርገው መንግሥትን ነው፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

የሰሜኑ ጦርነት እና ያልተቋረጡት ውዝግቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:11 0:00

XS
SM
MD
LG