የእስራኤል ወታደሮች የፍልስጤም ታጣቂዎች ናቸው ብለው የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች መግደላቸውን የእስራኤል ፍልስጤም ሪፖርት አመላከተ።
እስራኤል በሰሜናዊ ዌስት ባንክ ባደረገችው የሌሊት ፍተሻ ላይ የተሰማሩ ሰራዊቶች፤ በተልዕኮ ላይ ሳሉ በናቡላስ ከተማ አቅራቢያ በመኪና እና በሞተር በመሆን በቡድን የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ማየታቸውን እና ተኩስ መክፈታቸውን አስታውቀዋል።
የአንበሳ ዋሻ በሚል የሚጠራው የአካባቢው ታጣቂ ቡድን ሳይድ አል-ኩኒ የተሰኘው አባሉ 'ተልዕኮ ላይ ከነበረው ሃይል ጋር በተፈጠረው ግጭት' ሕይወቱ አልፏል ሲል አስታውቋል።