በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ አምስት ፍልስጤማውያን ላይ የሞት ቅጣት ተፈጸመ


General view of Gaza city
May 29,2022
REUTERS/Mohammed Salem/File Photo
General view of Gaza city May 29,2022 REUTERS/Mohammed Salem/File Photo

በሃማስ አስተዳደር ስር ባለቸው ጋዛ አምስት ፍልስጤማውያን ዛሬ የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል። በሞት ከተቀጡት ሁለቱ፣ ከዓመታት በፊት ለእስራኤል ትሰልላላችሁ ተብለው ክስ የቀረበባቸው ናቸው። ሶስቱ ደግሞ ሰው በመግደላቸው ነው ተብሏል።

ዛሬ ማለዳ በስቅላት ወይም በአልሞ ተኳሽ ተፈጽሟል የተባለው ቅጣት ከአምስት ዓመታት ወዲህ በፍልስጤም ግዛት የተፈጸመ የሞት ቅጣት ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፣ በስለላ ጥፋተኛ የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች ለእስራኤል መረጃ በመስጠታቸው ፍልስጤማውያን እንዲገደሉ ምክንያት ሆነዋል ብሏል።

የሞት ቅጣቱ የተፈጸመው ሁሉም የህግ ሂደቶች ከተጠናቀቁ በኋላ መሆኑንና፣ ተከሳሾቹ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሙሉ መብት እንደተሰጣቸው፣ እንዲሁም ውሳኔው የመጨርሻ እንደነበር መግለጫው ጨምሮ ገልጿል። የሮይተርስ ዘገባ የተባለውን ማጣራት እንዳልቻለ ጠቁሟል።

የፍልስጤምና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሞት ቅጣቱን አውግዘው፤ ሃማስና፣ በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክ የተወሰነ የራስ ገዝ ስልጣን ያለው የፍልስጤም አስተዳደር የሞት ቅጣትን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

የፍልስጤም ህግ ፕሬዝደንት ማህሙድ አባስ የሞት ፍርድን የማጽደቅ ወይም የመሻር ስልጣን ቢሰጣቸውም፣ ጋዛን በተመለከተ ግን ምንም ስልጣን የላቸውም።

እስላማዊው ሃማስ ጋዛን ከተቆጣጠረበት እ.አ.አ 2007 ጀምሮ እስከ አሁን 27 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ፈጽሟል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ይገልጻሉ።

XS
SM
MD
LG