በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ እና የቻይና ድፕሎማቶች በታይዋን ምክንያት በተፈጠረው ውጥረት ዙሪያ ተወያዩ 


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ከቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77ኛ ጉባኤ ላይ ሲገናኙ 
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ከቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77ኛ ጉባኤ ላይ ሲገናኙ 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን እና የቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ አርብ እለት ተገናኝተው፣ በተለይ ውጥረት በሚኖርበት ወቅት በቤይጂንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ግንኙነት ለመቆጣጠር ግልፅ የሆነ የግንኙነት መስመር ሊኖራቸው እንደሚገባ ተወያይተዋል።

የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማቶች በኒው ዮርክ በተካሄደው 77ኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ ብሊንከን "በመላው ታይዋን ሰላም እና መረጋጋትን መኖሩ ለቀጠናው እና ለዓለም ደህንነት እንዲሁም ብልፅግና እጅግ ወሳኝ መሆኑን" አፅንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫም "አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ በጣም የተሳሳተ እና አደገኛ መልዕክት እያስተላለፈች" መሆኑን ገልፆ ታይዋን ለነፃነት የምታደርገው እንቅስቃሴ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ቁጥር ሰላማዊ መፍትሄ ማግኘት የበለጠ አዳጋች ይሆናል ብሏል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ "የታይዋን ጉዳይ የቻይና የውስጥ ጉዳይ መሆኑን እና ዩናይትድ ስቴትስ ችግሩን ለመፍታት ምን መንገድ መከተል እንዳለብን ጣልቃ የመግባት መብት እንደሌላት" መናገራቸውንም የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ያወጣው መግለጫ አክሎ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG