ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ የመጀመርያ ሪፖርቱን ትናንት ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አቅርቧል።
በምክር ቤቱ የተቋቋመው የባለሙያዎች ኮሚሽን የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጫረ አንስቶ በሁሉም ወገኖች ሰፊ ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘቱን ቢገልፅም ለአብዛኞቹ ወንጀሎች ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሆነ ተናግሯል።
ህወሓት እራሱን ከሚመለከተው ክፍል በስተቀር ሪፖርቱን እንደሚቀበለው ያመለከተ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ማለዳ ላይ ‘መቀሌ ላይ ተፈፀመ’ ባለው የአየር ጥቃት አንደ ሰው መገደሉን የፈረንሣይ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
በሌላ በኩል ጦርነቱ ቆሞ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና 72 አባላት ያሉት የሲቪል ማኅበራት ኅብረት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]