በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋር ክልል ለግብረሰናይ ድርጅቶች የእርዳታ ጥሪ አቀረበ


የአፋር ክልል ለግብረሰናይ ድርጅቶች የእርዳታ ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:42 0:00

የአፋር ክልል ለግብረሰናይ ድርጅቶች የእርዳታ ጥሪ አቀረበ

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ ድጋፍ ማኅበረሰብ እንደገና በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ለሶስተኛ ጊዜ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ እንዲያደርግ የአፋር ክልል ጥሪ አአቅርቧል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሑሴን፣ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት 107 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀው፣ ክልሉ የቻለውን ያህል እርዳታ እያቀረበላቸው ቢሆንም በቂ አይደለም ብለዋል፡፡

ሰዎቹ ለሦስተኛ ጊዜ የተፈናቀሉ በመሆናቸውም የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

እንደገና በተጀመረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ከአፋር ክልል የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ያረጋገጠው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ዩኤንኦቻ) በጎርፍ ምክንያት ደግሞ 59 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG