በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በአዋሽ ሰባት የተያዙ ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት በአፋጣኝ ሊከበር ይገባል” ኢሰመኮ


“በአዋሽ ሰባት የተያዙ ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት በአፋጣኝ ሊከበር ይገባል” ኢሰመኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

“በአዋሽ ሰባት የተያዙ ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት በአፋጣኝ ሊከበር ይገባል” ኢሰመኮ

ከትግራይ ክልልና ከአዋሳኝ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዋሽ ሰባት የተያዙ ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት በአፋጣኝ ሊከበር ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል።

ሰዎቹ በደቡብ ወሎ ዞን ጃሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሰው ኮሚሽኑ፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ወደ አዋሽ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲዛወሩ መደረጋቸውን አመልክቷል።

በአሁኑ ጊዜ ሰዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመከታተል ኮሚሽኑ በአዋሽ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ጉብኝት ለማካሔድ ያደረገው ጥረት እስካሁን እንዳልተሳካለትም ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ፖሊስን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በሌላም በኩል በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት 30,000 ሰዎች አብዛኛዎቹ ከተበታተኑበት ወደ መጠለያው ጣቢያ መመለሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታውቋል ።

ተፈናቃዮቹ መጠለያውን ትተው የወጡት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንደገና መጀመሩን ተከትሎ ነበር።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG