በትግራይ ክልል ከነበሩ ከሰማኒያ በላይ የመድሃኒት ጅምላ አከፋፋይ ተቋማት መዘጋታቸውን የክልሉ የፋርማሲ ማኅበር ገለጸ፡፡ ወደክልሉ የሚገባ መድሃኒት ባለመኖሩ ህዝቡ ችግር ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡
“የዕርዳታ ሰጪ ተቋማት የሚያስገቡት መድሃኒት ከሚፈለገው መጠን አምስት ነጥብ ሁለት ከመቶ ብቻ ነው” ብሏል፡፡
ቀደም ሲል ተቋርጦ የነበረው የመድኃኒት የህክምና መገልገያዎች አቅርቦት ካለፈው ታኅሳስ አጋማሽ አካባቢ አንስቶ በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አማካይነት እንደገና ከገባ ወዲህ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት አፋጣኝ ዕርዳታ ድርጅት (ዩኒሴፍ)ን በመሳሰሉ ተቋማት አማካይነት ወደ መቀሌ መድረስ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ፌዴራል መንግሥቱና ህወሓት የሚወነጃጀሉበት ጦርነት ባለፈው ወር (ነኀሴ) አጋማሽ ሲያገረሽ መስተጓጎሉ ይታወሳል።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]