በዓለማችን ረጅም ዘመን በንግሥና መንበር የቆዩት ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከአምስት መቶ በላይ የዓለም መሪዎች፣ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል።
በእንግሊዝ ነገሥታት ታሪክ ከ70 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ብሄራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት እጅግ በርካታ ዓለም አቀፍ ሪኮርዶችን እንደሚሰብርም ተጠብቋል።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱን የተከታተለው የለንደን ዘጋቢያችን አስተዋይ መለስ ነው።