በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ተወላጆች የነበሩበት የሠመራ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ


የትግራይ ተወላጆች የነበሩበት የሠመራ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:46 0:00

የትግራይ ተወላጆች የነበሩበት የሠመራ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ

በአፋር ክልል የትግራይ ተወላጆች ለስምንት ወራት ያህል ተይዘውበት የነበረው የሠመራ ካምፕ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

የአፋር ክልላዊ መንግሥት በሠመራ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የነበሩትን ሰዎች በኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ መሰረት እንዲለቀቁ በማድረጉ ኮሚሽኑ እውቅና የሚሰጥ መሆኑንም ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ዙሪያ ለቪኦኤ ማብራሪያ የሰጡት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞች፣ የተፈናቃዮችና የፍልሰተኞች መብቶች የሥራ ክፍል ተጠባባቂ ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ የአፋር ክልላዊ መንግሥት የኮሚሽኑን ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ በመተግበር ረገድ ለሌሎች አርአያ ይሆናል ብለዋል፡፡

የአፋር ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ በሠመራ ካምፕ የነበሩትን ሰዎች ወደ መኖሪያቸው የመመለሱ ሥራ ቀድሞ በተያዘ እቅድ መሰረት የተከናወነ እንጂ በኮሚሽኑ ምክረ ሀሳብ መሰረት የተፈፀመ እንዳልሆነ ገልፆዋል፡፡

በክልሉ በአጋቲና ካምፕ የሚገኙትን 600 ሰዎችም በፍላጎታቸው መሠረት ወደ ትግራይ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG