በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜኑ ጦርነት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ህወሓት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች አስተያየቶች


በሰሜኑ ጦርነት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ህወሓት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች አስተያየቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00

በሰሜኑ ጦርነት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ህወሓት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች አስተያየቶች

“ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሠላም ሂደት ቁርጠኛ ነች” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ ይህን ያሉት በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከሆኑት ሪታ ላራንጂንሃ ጋር ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ “የአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚቀበል” ህወሓት ላሳወቀው አቋም አቶ ደመቀ ምን ምላሽ እንደሰጡ የተባለ ነገር የለም፡፡

በተያያዘ ዜና የአውሮፓ ሕብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ሁለት ቀናት በመቀሌ የፈጸመው የድሮን ጥቃት፣ ህወሓት የአፍሪካ ኅብረትን የሠላም ሂደት እንደሚቀበል ማሳወቁን ተከትሎ “በኢትዮጵያ ለሠላም ያለውን ጭላንጭል ተስፋ ዳግም አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ብሏል፡፡

የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሠላም ጥሪ ማቅረባቸውን የቀጠሉ ቢሆኑም፣ ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ጦርነቱ አሁን የሚገኝበትን ደረጃ አስመልክቶ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄነራል

ታደሰ ወረደ ማክሰኞ ዕለት ለክልሉ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር ሽራሮን እና አካባቢውን መቆጣጠሩን ገልጸዋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG