በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜኑ ጦርነት እና እያነጋገሩ ያሉት ጉዳዮች


የሰሜኑ ጦርነት እና እያነጋገሩ ያሉት ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00

የሰሜኑ ጦርነት እና እያነጋገሩ ያሉት ጉዳዮች

ህወሓት በአፍሪካ ሕብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ካሳወቀ በኋላም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቀጠሉ እየተነገረ ነው። ጦርነቱ ዛሬም መቀጠሉን በትዊተር ገጻቸው የገለጹት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በመቀሌ ከተማ የድሮን ጥቃት መፈጸሙንም አመልክተዋል፡፡

ጥቃቱ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አዲ ሃቂ ግቢ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ቢገልጹም፣ በጥቃቱ ስለደረሰ ጉዳት ግን ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡

በሌላ በኩል የድሮን ጥቃት የተፈጸመው በሁለት ተቋማት ላይ እንደሆነ የቪኦኤው የመቀሌ ዘጋቢ የላከው ዘገባ ያመለክታል፡፡

ዛሬ ተፈጽሟል የተባለውን የድሮን ጥቃት በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ ባይሰጥም፣ መንግሥት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ክሶችን አስተባብሏል።

በተያያዘ ዜና፣ ዋይት ሃውስ ትናንት በሰጠው መግለጫ፣

“ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚደረገውን ውይይት ላይ ለመሳተፍ እና ጦርነቱን ለማቆም ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ ያወጣውን መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ በደስታ እንደምትቀበል” በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር እስካሁን በቀጣናው እንደሚገኙም የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ለህወሓት መግለጫ ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ሄርማን ኮህን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት አስተያየት፣

“ህወሓት ከአፍሪካ ህብረት የሰላም ሂደት መጠበቅ የሚችለው የተሻለው ነገር እንቅስቃሴውን ማፍረስ እና ለአመራሮቹ ምህረት ማግኘት ነው” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG