በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድና ቻይና ወታደሮቻቸውን ከተወዛገቡበት ድንበሮቻቸው አራቁ

FILE- An Indian schoolgirl wears a mask of Chinese President Xi Jinping to welcome him on the eve of his visit in Chennai, India, Oct. 10, 2019.
FILE- An Indian schoolgirl wears a mask of Chinese President Xi Jinping to welcome him on the eve of his visit in Chennai, India, Oct. 10, 2019.

ህንድና ቻይና በሂማሊያ ተራራዎች አካባቢ ለሁለት ዓመታት ከተወዛገቡባቸው በርካታ የድንበር አካባቢዎች ወደ የኋላቸው ማፈግፈጋቸው ተነገረ፡፡

የህንድ መካለካያ ሚኒስቴር ትናንት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ ወታደሮቹ ጎርጋ ከተባለው የፍልውሃ አካባቢ “በተቀናጀና በታቀደ መንገድ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በጠበቀ መንገድ ከድንበር አካባቢዎቹ ለቀው ወጥተዋል ሲል አስታውቁል፡፡

መግለጫው የወጣው በ2013 በምዕራብ ሂማሊያ ላዳክ በተባለው አካባቢ በደረሰ ግጭት 20 የህንድና ሁለት የቻይና ወታደሮች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ እየተባባሰ የመወጣው ወታደራዊ ፍጥጫ ሲካሄድ ከቆየ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሁለቱ አገሮች በድንበሮቻቸው አካባቢው እያንዳንዳቸው በተዋጊ ጀቶች ታንኮችና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎች የታገዙ ከ50ሺ ወታደሮች በላይ ማስፈራቸው ሲነገር መቆየቱ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG