በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጎርፉ ከጋምቤላ ህዝብ ሃምሳ ከመቶውን ማፈናቀሉን ክልሉ አስታወቀ


ጎርፉ ከጋምቤላ ህዝብ ሃምሳ ከመቶውን ማፈናቀሉን ክልሉ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

ጎርፉ ከጋምቤላ ህዝብ ሃምሳ ከመቶውን ማፈናቀሉን ክልሉ አስታወቀ

በጋምቤላ ክልል ባለፈው ነሐሴና በዚህ የጳጉሜ ወር እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከክልሉ ነዋሪዎች 50 በመቶ የሚሆኑት መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ እንዳሉት እስካሁን 187 ሺ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በላሬ ወረዳ ደግሞ 2 በዕድሜ የገፉ ሰዎችና አንድ ሕጻን በአጠቃላይ ሦስት ሰዎች በጎርፉ ሳቢያ መሞታቸውን አስታውቀዋል።

መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመደገፍ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ባለሥልጣኑ ሆኖም እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ህዝቡም ለመርዳት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG