በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ በ 96 ዓመታቸው ዛሬ አርፈዋል


People takes photos of an image of Queen Elizabeth displayed at Piccadilly Circus n London, after she died, Sept. 8, 2022. (Reuters)
People takes photos of an image of Queen Elizabeth displayed at Piccadilly Circus n London, after she died, Sept. 8, 2022. (Reuters)

ለ 70 ዓመታት ዙፋን ላይ የቆዩት የእንግሊዟ ንግሥት ዛሬ ስኮትላንድ በሚገነኘው መኖሪያ ቤታቸው እንዳሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ንግሥቲቱ ሰሞኑን የጤናቸው ሁኔታ ጥሩ ባለመሆኑ በሃኪሞች የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር። ንግስቲቱ ከሁለት ቀናት በፊት፤ ማክሰኞ አዲሷን የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስትር ሊዝ ትረስ ሹመትን ለማጽደቅ ስኮትላንድ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አግኝተዋቸው ነበር። ጠቅላይ ምኒስትሯ የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ዛሬ ጠዋት ተናግረው ነበር።

ንግሥት ኤልሳቤጥ በእንግሊዝ ንጉሣዊ አገዛዝ ታሪክ ለረጅም ዘመን የነገሡ ናቸው። ይህም ከቅም አያታቸው ከንግሥት ቪክቶሪያ ቀጥሎ ረጅሙ የንግሥና ዘመን መሆኑ ነው።

ንግሥት ኤልሳቤጥ ዙፋኑን ይቆናጠጣሉ ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። ከ86 ዓመት በፊት ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ፣ ዋሊስ ሲምፕሰን የተባለች ታዋቂ አሜሪካዊ ለማግባት ሲወስኑ ዙፋኑን ለቀዋል። የንሥቲቱ አባት ንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ ዙፋኑን ሲረከቡ፣ ኤልሳቤጥን ለንግሥትነት ቅርብ አደረጋቸው።

ልጃቸው ለዑል ቻርለስ፤ አሁን ንጉሥ ቻርለስ፣ በቅርቡ በሚደረግ ሥነ-ስርዓት ዙፋኑን ይረከባሉ። በዓለ ንግሥቸው ግን ትንሽ ግዜ እንደሚወስድ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG