በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኤርትራ ሠራዊት በተለያዩ ግንባሮች ጥቃት እያደረሰ ነው” ሲል ህወሓት ከሰሰ


ኢትዮጵያ እና ኤርትራ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ

“ማንኛውንም የሰብአዊ እርዳታ ሥርቆት በተመለከተ የሚነሳ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተን እንመለከታለን፣ የሚቀርቡ ክሶችን እንመረምራለን” ሲል ዩኤስኤአይዲ አስታወቀ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮ በትዊተር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሲቪል ኢትዮጵያውያን በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸም የሰብዓዊ እርዳታ ሥርቆትን” እናወግዛለን ብሏል።

በሌላ ተያያዥ ዜና፣ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጳጉሜ 2 በትዊተር ገጻቸው ባቀረቡት ክስ “የኤርትራ ሰራዊት በተለያዩ ግንባሮች ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል። የአዲግራት ከተማ ዳርቻዎችን ሲደበድብ ውሏል” ሲሉ ወንጅለዋል፡፡

ይህን ክስ በተመለከተ ከኤርትራ መንግሥት እስካሁን የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ የለም፡፡

ይሁንና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል “በኤርትራ የሥርዓት ለውጥ የማምጣት ዕቅድ አለው” ሲሉ ህወሓትን ከስሰዋል፡፡

ከተቀሰቀሰ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም እና የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ በመጣር ላይ የምትገኘው ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኳን ወደ ኢትዮጵያ ከላከች ቀናት ቢቆጠሩም ስለኢትዮጵያ ጉብኝታቸው እስካሁን የወጣ መረጃ የለም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።

“የኤርትራ ሠራዊት በተለያዩ ግንባሮች ጥቃት እያደረሰ ነው” ሲል ህወሓት ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00

XS
SM
MD
LG