በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ ሦስት ምርመራዎች


የትረምፕ ሦስት ምርመራዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:42 0:00

የትረምፕ ሦስት ምርመራዎች

የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ቤት ድንገት ከበረበረ አንድ ወር ተቆጠረ።

“ፓልም ቢች፣ ፍሎሪዳ ያሚገኘው ቆንጆ ቤቴ በርከት ባሉ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ሰዎች ተወሮ ተይዟል” ብለው ነበር ትረምፕ በዕለቱ።

“ከመንግሥት አካላት ጋር ትብብር ካሳየሁ በኋላ፣ ቤቴን መውረሩ አስፈላጊ እና ተገቢ አይደለም” ሲሉም አክለዋል።

በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የብሄራዊ መዛግብት አስተዳደር ከፍተኛ ምስጢር ጭምር የያዙ 15 ካርቶን ሰነዶችን በትረምፕ መኖሪያ ቤት ካገኘ በኋላ፣ ጉዳዩን ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ሹክ ብሏል። ትረምፕ እነዚህን ሰነዶች ለብሄራዊ መዛግብት አስተዳደር ቢመልሱም፣ መርማሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው ባደርጉት ምርመራ ያልተመለሱ ዶሴዎችን በካዝና ውስጥ አግኝተዋል።

በእአአ 1978 የወጣውና ፕሬዚዳንታዊ መዛግብትን የሚመለከተው ደንብ እንደሚገልጸው፣ ፕሬዚዳንቶች በሥራቸው አጋጣሚ እጃቸው የሚገባው መዛግብት የህዝብ ንብረት በመሆኑ ወደ ብሄራዊ መዛግብት አስተዳደር ገቢ መደረግ አለባቸው።

ከሁለት ዓመት በፊት በተደረገው ምርጫ ሥልጣናቸውን የተነጠቁት ትረምፕ፣ ነጩን ቤተ መንግሥት ሲለቁ፣ ምስጢራዊ ሰነዶችን ወስደው ፍሎሪዳ ወደሚገኘው ቅንጡ ቤታቸው ደብቀዋል።

የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ ባለፈው ወር ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ “ምስጢር” እና “ከፍተኛ ምስጢር” የሚል ምልክት የተደረገባቸው በመቶ የሚቆጠሩ ገጾች ያሏቸውን 13 ካርቶን ዶሴዎች አግኝቷል።

የፍትህ መሥሪያ ቤቱ በትረምፕ እጅ ተገኝተዋል የተባሉ ምስጢራዊ ዶሴዎችን ከመመርመሩ በተጨማሪ፣ በፈርንጆቹ ጥር 6/2021 የተፈጸመውን የምርጫ ውጤት ለመገልበጥ የተደረገውን ሙከራም በመመርመር ላይ ነው።

የአሜሪካ ምክር ቤት አንድ ኮሚቴ በማቋቋም ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ምስክሮችን ሲያደምጥ ቆይቷል። የትረምፕ አስተዳደር ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ባለሥልጣናት ሳይቀሩ በቀድሞ አለቃቸው ላይ መስክረዋል።

ከነዚህ ሁለት ምርመራዎች በተጨማሪ፣ በእአአ 2024 ለፕሬዚዳንትነት እንደገና ለመወዳደር በሚሹት ዶናልድ ትረምፕ ላይ እየተካሄደ ያለ ሌላ ሦስተኛ ምርመራ አለ።

ጆርጂያ ግዛት በሚገኙ አቃቤ ህግ በመካሄድ ላይ ያለው ይህ ምርመራ “ምርጫ ለማጭበርበር በማሰብ ሰዎችን ትብብር ጠይቀዋል” በሚል ነው።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG