በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በሰቆጣ ወረዳ 10 ሰዎች በህወሓት ጥቃት ተገደሉ” የዞኑ አስተዳደር እና ቤተሰቦች


“በሰቆጣ ወረዳ 10 ሰዎች በህወሓት ጥቃት ተገደሉ” የዞኑ አስተዳደር እና ቤተሰቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00

“በሰቆጣ ወረዳ 10 ሰዎች በህወሓት ጥቃት ተገደሉ” የዞኑ አስተዳደር እና ቤተሰቦች

በአማራ ክልል፣ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ሰቆጣ ወረዳ ልዩ ስሙ ወለህ ማሪያም በተባለ ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 10 ንጽሀን ዜጎችን ከህወሓት ተተኮሰ በተባለ ከባድ መሳሪያ መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር እና የሟቾቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል ።

ከሟቾቹ መካከል በቅርቡ የተዳረች ሙሽራ እንደምትገኝበት የዞኑ የኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከፍያለው ደበሽ ጠቁመዋል።

ከነዚህ የአንድ ቤተሰብ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ወጣቶች በህወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውን በመግለፅም ወንጅለዋል።

ከህወሓት በኩል በዚህ አዲስ ጥቃት ዙሪያ የተሰማ ቀጥተኛ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል የተሰነዘሩ መሰል ውንጀላዎችን ንጹሐንን ኢላማ እንደማያደርግ በመግለፅ አስተባብሏል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ተዋጊዎቻቸው ሕዝብን ኢላማ እንደማያደርጉና የተማረኩ ታጣቂዎችን ሳይቀር በተገቢው መንገድ እንደሚይዙ ተናግረዋል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG