በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ከፍተኛ የርዕደ መሬት አደጋ ደረሰ


በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ከፍተኛ የርዕደ መሬት አደጋ ደረሰ
በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ከፍተኛ የርዕደ መሬት አደጋ ደረሰ

በቻይና ደቡባዊ ምስራቅ ክፍለ ግዛት ዛሬ ሰኞ እኩለ ቀን ላይ በተከሰተ ርዕደ መሬት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

በሬክተር ስኬል ሲለካ 6.8 መሆኑ የተገለጸው የርዕደ መሬት አደጋው የደረሰው ብዙ ጊዜ በሚታይበት ሲሿን ክፍለ ግዛት መሆኑ ተዘግቧል፡፡

በአደጋው ሳቢያ በደረሰ የመሬት መንሸራተት መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና ኃይል መቋረጡን የመንግሥት ዜና ማሰራጫ ሲሲቲቭን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከደረሰበት ስፍራ፣ 200 ኪሎ ሜትሮች ርቀት በምትገኘው የክፍለ ግዛቲቱ ዋና ከተማ ድረሰ ዘልቆ መሰማቱም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ግንቦት 4 ቀን 2000 ዓም በሲሿን ደርሶ በነበረው የ8.0 ሬክተል ስኬል ርዕደ መሬት አደጋ ወደ 7ሺ ሰዎች መሞታቸው ከአሶሼይትድ ፕሬስና ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተገኙ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG